
አዲስ በመሠራት ላይ የሚገኘው በሀገረ ስብከቱ ምክረ አሳብ መጠነኛ የዲዛይን ማሻሻያ በባለሙያዎች የተደረገበት የጅንካ አንቀጸ ብጹአን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የአብነት ተማሪዎች እና የስብከተ ወንጌል ማሰልጠኛ ዲዛይን ይህንን ይመስላል፡፡
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ የሀገረ ስብከቱን ካህናት በቋንቋ የሚያስተምሩ ሰባክያነ ወንጌል ችግር ይፈታል ተብሎ ታምኖበት በማሠራት ላይ ያለው ይህ ህንጻ የመጀመሪያ ዙር ሥራ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚህ ዓመት ማለትም 2011 ዓ.ም መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሎ ዕቅድ ተይዞለት እየተፋጠነ ይገኛል፡፡
ይህ የማሰልጠኛ ህንጻ ሲጠናቀቅ አሁን ተማሪዎቹ ከሚማሩበት ፍጹም ምቹ ካልሆነ እና ለትምህርትም አስቸጋሪ ከሆነ ማደሪያ ይወጣሉ ለትምህርታቸውም ምቹ የሆነ ሁኔታ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ተጠናቆ እንድናየው የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን፡፡


