ቀኑ ደረሰ በቀሩት ቦታዎች ፈጥናችሁ ተመዝገቡ በጉዞዋችን የኦሞን ወንዝ ተሻግረን ኬንያ ድንበር ላይ ቃለ እግዚአብሔር ይሰበካል፡፡ቡስካ ተራራ ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ በስሙ በብቸኝነት የሚገነባው ታላቅና ድንቅ የቅዱስ አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም በቡስካ ተራራ ላይ ይጎበኛል፡፡ ኑ!! ወደ ደቡብ ኦሞ እንጓዝ! መነሻ ቀን ቅዳሜ የካቲት 14/2012 መመለሻ የካቲት 20/2012 አሁኑኑ ይመዝገቡ

እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!!

የጂንካ ቅድስት በአታ ለማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን የግንባታ ሥራው እንዲህ በአማረ መልኩ ተጠናቅቆ  ዛሬ የካቲት 8/2012 ዓ.ም

  1. ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የበላይ ሊቀ ጳጳስ
  2. ብጹዕ አቡነ ናትናኤል የወለጋ ሁሩጉዱሩ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ
  3. ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚዲያ የበላይ ሊቀጳጳስ የጠቅላይ ቤተክህነት የስብከተ ወንጌል መምሪያ ሊቀጳጳስ
  4. ብጹዕ አቡነ አረጋዊ የጠቅላይ ቤተክርህነት የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሊቀጳጳስ እንዲሁም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተመርቋል፡፡

ይህንን የመሰለ ውብ ቤተክርስቲያን ለመስራት ገንዘቡን ጉልበቱን እና ጊዜውን ለመስጠት ያልሰሰተ የጅንካ ህዝበ ክርስቲያን ሊመሰገን ይገባዋል፡፡የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ምንም ትኩረቱ በገጠሪቱ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ቢሆን በህንጻ አሰሪ ኮሚቴው በተጠየቀው ድጋፍ መሰረት የበኩሉን በማድረግ ከቅድስት በአታ በረከት በመሳተፉ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!