እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ልማት ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በየዓመቱ እንደሚያደርገው ዘንድሮም የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በዚህ ዓመት የተከናወኑትን አዳዲስ ድንቅ ድንቅ ተግባራትን አክሎ ዐውደ ርእይ በነጻ በጃንሜዳ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል፡፡
የሻንቆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተመረቀ
እንኳን ደስ አላችሁ!
እነሆ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሻንቆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ህዳር 6 ቀን 2011 ዓ.ም በሶስት ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ማለት በብጹዕ አቡነ ዕንባቆም በቅድስት ሀገረ ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ገዳማት ሊቀጳጳስ በብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተባርኮ ተመርቋል፡፡
የካህኑ ትልቅ መልእክት
ልዩ የሲዲ ምረቃ
በእህታችን ሲስተር ፋሲካ መኮንን የተዘጋጀው ሲዲ ገቢው ለደቡብ ኦሞ ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ አገልግሎት የሚውለው “ጸጋ ነሳእነ” ካሴት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ይመረቃል፡፡
አርብ ሚያዚያ 12 ቀን2010 ዓ. ም በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም ቅዳሜ ሚያዚያ 13 ቀን በቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሲዲውየሚመረቅ ሲሆን አውደ ርዕዩ በዚያው በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ለሶስት ቀናት (ከሚያዚያ 12-14/2010 ዓ. ም) የሚቆይ ይሆናል፡፡
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት አገልግሎት ደጋፊዎችና አባላት እንዳትቀሩ አደራ
የኮሚቴው አመራሮች በቴሌቭዥን “ዕድሜን ለበረከት”
እነሆ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አመራር አካላት የኮሚቴውን ጠቅላላ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ዕሁድ ሚያዚያ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቭዥን \”ዕድሜን ለበረከት\” በሚል ፕሮግራም ላይ የክብር እንግዶች ሆነው በመቅረብ ኮሚቴውን አስመልክቶ ሰፊ ገለጻ ይሰጣሉ፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጅ፡- መምህር ኃይሉ
በመሆኑም የኮሚቴው አባላትና ደጋፊዎች የትንሳኤን በዓል እያከበራችሁ የኮሚቴውን መርሐ ግብር እንድታከታተሉንና ለሌሎች እህት፥ ወንድሞቻችንም እንድትጋብዙልን እንጠይቃለን።
መልካም የሰሞነ ሕማማት ጊዜ እንዲሁም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
1464 ምዕመናንን ተጠመቁ
እንኳን ደስ አላችሁ!
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ኮሚቴ ከየካቲት 14-22/2010 ዓ.ም ባደረገው መንፈሳዊ ጉዞ 1464 ምዕመናንን በተለያዩ ቦታዎች አጠመቀ፡፡
በነምረሙዝ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ዓመታዊ በዓሏ በተከበረት ዕለት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ በተገኙበት 1024 የዳሰነች ብሔረሰቦች የተጠመቁ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ በሐመር በሸዳ እንዲሁም በአርኪ ቅዱስ ገብርኤል በዓል ምረቃ ዕለት የተጠመቁ ናቸው፡፡
ዜና ሲመተ ክህነት
በጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም እና በተለያዩ አጥቢያዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ ቆይተው ለሲመተ ክህነት የሚያበቃቸውን የአብነት ትምህርት ያጠናቀቁ ደቀ መዛሙርት 65 ዲያቆናት እና 8 ቀሳውስት በትላንትናው ዕለት ከብፁእ አባታችን አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አንብሮተ እድ በጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተሹመዋል ።
Continue reading “ዜና ሲመተ ክህነት”አዳዲስ ምዕመናን ተጠመቁ
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከት ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በዳሰነች ወረዳ በነምረሙስ ቅድስት ኪዳነ ምህረትና በበሸዳ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያ ባዘጋጀው የጥምቀት ፕሮግራም ላይ በነምረሙዝ 1537 በበሸዳ 117 አዲስ አማንያን በድምሩ 1654 ምዕመናን ወደዚህ ቤተክርስቲያን ህብረት ተቀላቅለዋል፡፡
READ MOReየሰልጣኞች ምርቃት
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ከነሀሴ 22-27/2009 ዓ.ም ለስድስት ቀን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ያሰለጠናቸውን 84 ወጣቶች አስመረቀ፡፡
ይህ ስልጠና በደቡብ ኦሞ በቋንቋ ለሚሰብኩ ወጣቶች የተዘጋጀ የማነቃቂ ስልጠና እንደሆነ የንኡስ ኮሚቴው ሰብሰባ ተናግረዋል፡፡
Continue reading “የሰልጣኞች ምርቃት”ታላቅ አውደ ርእይ በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አትሮኖስ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ክፍል ያዘጋጅው ዐውደ ርእይ ነሐሴ 11 ቀን 2009 ዓ.ም በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህርት የገደሙ አለቃ ተባርኮ ተከፈተ።
አውደ ርእይ እስከ ነሐሴ 15 2009 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በመሆኑ እንድትጎበኝ ተጋብዛችኃል፡፡




