በደቡብ ኦሞ ለሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ለቋንቋ መምህራን የሁለት ቀን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ኮሚቴ አስተባባሪነት የማንቂያ ደወል ስልጠና ከህዳር 7-8/2013 ዓ.ም በጅንካ ተሰጠ፡፡
ስልጠናው ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማንቃትና ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ አገልግሎ መስጠት የሚችሉበትን ሥራ መስራት እና የእርስ በእርስ ትስስርን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነበር፡፡
በስልጠው የምዝጊያ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ መንክራት ቆሞስ አባ ስምረት አብ ባስተላለፉት መልእክት ሰልጣኞቹ የተሰጣቸውን ስልጠና ተጠቅመው ሌሎችን ደግሞ በየሰንበት ትምህርት ቤቱ ማንቃት እንዳለባቸውን ወቅቱን ያገናዘበ ስልጠና በእዚህ መልክ ኮሚቴ በተከታታይነት ማዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡









