ታላቅ አውደ ርእይ በላፍቶ ደብረ ኢያሪኮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

እኛም ጥምቀትና ቤተክርስቲያን እንፈልጋለን!!

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ልማት ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በደብረ ኢያሪኮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በሰበካ ጉባኤው መልካም ፈቃድ የመድኃኒዓለም ዓመታዊ በአልን ምክንያት በማድረግ ከዋዜማው ረቡዕ ጥቅምት 26/2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዕሁድ ጥቅምት 30/2012 ዓ.ም ለአምስት ቀን  የሚቆይ ልዩ አውደ ርእይ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል፡፡

ከዚህ በፊት ይህ ልዩ አውደ ርእይ ወደ እዚህ ቤተክርስቲያን ይዘን እንድንመጣ ስትጠይቁ የነበራችሁ የኮሚቴው አባላትና የዓላማው ደጋፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፡፡

በእነዚህ ቀናቶች እየተገኛችሁ እግዚአብሔር በደቡብ ኦሞ እያደረገልን ያለውን ድንቅ ነገር እንድትመለከቱ እና ስለሆነው ሁሉ ልዑል እግዚአብሔርን እድታመሰግኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!!

ዐውደ ርእይ በጃንሜዳ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!
የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ልማት ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በየዓመቱ እንደሚያደርገው ዘንድሮም የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በዚህ ዓመት የተከናወኑትን አዳዲስ ድንቅ ድንቅ ተግባራትን አክሎ ዐውደ ርእይ በነጻ በጃንሜዳ አዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል፡፡

Continue reading “ዐውደ ርእይ በጃንሜዳ”

ልዩ የሲዲ ምረቃ

በእህታችን ሲስተር ፋሲካ መኮንን የተዘጋጀው ሲዲ ገቢው ለደቡብ ኦሞ ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ አገልግሎት የሚውለው “ጸጋ ነሳእነ” ካሴት ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ይመረቃል፡፡

አርብ ሚያዚያ 12 ቀን2010 ዓ. ም በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል እንዲሁም ቅዳሜ ሚያዚያ 13 ቀን በቦሌ መንበረ ብርሃን ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሲዲውየሚመረቅ ሲሆን አውደ ርዕዩ በዚያው በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ለሶስት ቀናት (ከሚያዚያ 12-14/2010 ዓ. ም) የሚቆይ ይሆናል፡፡

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት አገልግሎት ደጋፊዎችና አባላት እንዳትቀሩ አደራ