በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እነሆ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህጻና ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ጥቅምት 19 ቀን በ2009 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ኦሞ ቋንቋዎች በአሪኛ በሐመርኛ እና በማሌኛ ያዘጋጀውን መንፈሳዊ የመዝሙር ሲዲ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ያስመርቃል፡፡
ከዚያም በማያያዝ ከጥቅምት 20 ጀምሮ በተከታታይ አምስት አብያተክርስቲያናት እንዲሁ ያስመርቃል፡፡ የሚመረቁት አብያተክርስቲያናት
- የትነበርሽ ቅድስት ማርያም
- ተንቤን ቅዱስ ገብርኤል
- ኮመር ቅድስት አርሴማ
- ጎይረተር ቅድስት ኪዳነ ምህረት
- ወሰት ቅዱስ ሚካኤል ናቸው፡፡
ይህ የበረከት አገልግሎትና ምርቃት ለመሳተፍ በበአሉ ላይ ለመገኙት ከአዲስ አበባ ወደ ጅንካ ጉዞ ተዘጋጅቷል፡፡ጉዞ ከጥቅምት 18-27/2009 ዓ.ም ነው፡፡
ለመመዝገብ አሁኑኑ ወደ ኮሚቴው ቢሮ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 121 ቀርበው ይመዝገቡ
