የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ 1998 እስከ 2005 ዓ.ም

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከመዲናችን አዲስ አበባ 780 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በእጅጉ ቆላማ የሆነ እና ሁሉም የየራሳቸው የሆነ መገለጫ ቋንቋ፣ ባህል፣አለባበስ፣ አመጋገብ የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው የ16 ብሔረሰቦች መናኸሪያ ከመሆኑም ባሻገር መልክዐ ምድሩ እንደሰንሰለት የተያያዙና የተሰናሰሉ ተራሮች የሚበዙበት በቀላሉ በመኪና የማይደፈር ሀገረ ስብከት ነው፡፡

ብሔረሰቦቹ አኗኗራቸው የከብቶቻቸውን ጭራ ተከትለው የሚንቀሳቀሱ በተበታተነ ሁኔታ የወንዝን ተፋሰስ ተከትለው የሚያርሱ አርሶ አደሮች በመሆናቸው ከስልጣኔ ከትምህርት ከመሰረተ ልማት ርቀው ከመኖራቸው በተጨማሪ አካባቢያቸው ከመዳረሻ ከተማው ርቆ በበረሃማና ጠረፋማ ቦታዎች ላይ መሆኑ በቀላሉ ወደእዚህ ወገኖች ለመድረስ እጅግ በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ነው፡፡

እነዚህ ወገኖቻችን ምንም እንኳን በእንደዚህ ያለ አስቸጋሪ ቦታዎች ቢኖሩም የልባቸው ፍላጎትና መሻት ግን ከምድራዊ ይልቅ ለሰማያዊ ከስጋዊው ይልቅ ለመንፈሳዊው መሆኑን እና በክርስትና በሚገኘው ጸጋና በረከት ላይ መሆኑ ቀርቦ ለሚያ ሰው የእነዚህ ህዝቦች የክርስትና ፍላጎት የዛሬ ሳይሆን የትናንት የአሁን ሳይሆን የዘመናት መሆኑን ያሳያል፡፡

ለዚህ ማሳይ የሚሆኑት ደግሞ ከመካከላቸው ሰው ሲሞትባቸው የሞተባቸውን ሰው ነፍስ ቀን ቆጥረው መዘከራቸው የቀደሙት አባቶቻቸው ይነግሯቸው የነበረውን የመስቀል ምልክትነት ተስፋ አድርገው መስቀል የያዘ ካህን መጠበቃቸውና መስቀል የያዙ ካህናት ወደቀያቸው ሲመጡ የሚያደርጉላቸው አቀባበል ዝናብ ባጡባቸው ጊዜያት እንኳን ለዝናቡ መምጣትና ስለዝናብ በጸሎታቸው ተማምነው ጸልዩ ማለታቸው ሳይጠመቁና ሳይማሩ ወደ ቤተክርስቲያ ስለትና አምሀ ይዘው መምጣታቸው ነገ ቤተክርስቲያን ይሰራበታል በሚል ተስፋ የተቀመጠውን የመሰረት መስቀል ጎንበስ ብለው መሳለማቸው ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው፡፡

ይህን የሚያስረግጥልን ደግሞ ከአንደበታቸው የሚደመጠው ልብን የሚነካ የእምነት ቃላቸው ነው፡፡ ይኸውም \”ክርስትናን ባናውቀውም ልንኖርበት እንናፍቃለን ምክንያቱም የጥንቶቹ ቅዱሳን መልካም አሻራ ጥለውልን አልፈዋልና ስለዚህም ባንጠመቅም የሥላሴን ልጅነትን ባናገኝም የምናስቀድስበት የምንማርበት ስንሞትም ጸሎተ ፍትሀት ተደርሶ አጽማችን የሚያርፍበት ስንጨነቅ የምንጽናናበት ስንታመም የምንፈወስበት ከፈጣሪያችንም ጋር የምንገናኝበት ቤተክርስቲያን ባይኖረንም የጥንቶቹ አባቶቻችን ባሳደሩብን የክርስትና እና የእምነት ፍቅር ምክንያት ከተወለድን ጀምሮ ክርስቲያኖች ነን\”…….. ይላሉ፡፡

እነዚህ ወገኖቻችን ይህን ያህል የእምነት ጽናት የክርስትና ጥማት ቢኖራቸውም ካሉበት የቦታ ርቀትና ከመልካዐምድራዊ አቀማመጣቸው የተናሳ ያሉበት ድረስ ክርስትናው እና መምህራን ሳይደርሱላቸው ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ክቡር የሆነው የሥላሴ ፍጡር የወንጌልን የምስራች ሳይሰማ ሳያምን ሳይጠመቅ ሲሞት ጸሎተ ፍትሀት ሳይፈታ በደቡብ ኦሞ የትም ይጣል ነበር፡፡

በየጊዜውም አስተምሩን አጥምቁን የክርስቶስ ወገን አድርጉን ቤተክርስቲያን ስሩልን የሚለው የብሔረሰቦቹ ጥያቄ የሁላችንንም ውስጣዊ ስሜት የሚነካና እረፍት የሚነሳ ጉዳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ሀገረ ስብከቱ ትኩረት የሚሻ ሀገረ ስብከት መሆኑ ያመላክታል፡፡

ለዚህም ነው ቅዱስ ሲኖዶስ ለቦታ ትኩረት ሰጥቶ 1998 ዓ.ም ለዘመናት ከሰሜን ኦሞ ሀገረስብከት ጋር  ተደርቦ በሞግዚትናት በመተዳደር ቆይቶ የነበረውን ይህን ሀገረ ስብከት የራሱ የሆነ መንበረ ጵጵስና በዞኑ ዋና ከተማ ጅንካ ላይ በመትከል ብፁዕ አቡነ እንባቆምን የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አድርጎ በመሾም

እነዚህ ለዘመናት የተረሱ ህዝቦች የሚያነሱዋቸውን አስተምሩን አጥምቁን እንደ እናንተ የክርስቶስ ወገን አድርጉን ጥቄያ መልስ እንዲያገኝ ከፍተኛ ኃላፊነትን ሰጥቶ በቦታው ላይ መድቧቸዋል፡፡ ደቡብ ኦሞ ላይ ምን ሰሩ ይቀጥላል፡

ከ1998 ዓ.ም በፊት የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጋር በሞግዚትነት የሚተዳደር የነበረ በመሆኑ እና የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት በራሱ ሰፊ የቆዳ ስፋት የነበረውና የአቅም ውሱንነት የነበረበት በመሆኑ በደቡብ ኦሞ ጠረፋማና በረሃማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርሶ አደሮች ወገኖች ቤተክርስቲያን ከማነጽ ስብከተ ወንጌል ከማስፋፋት አንጻር ያን ያዕል ተደራሽ መሆን ለህዝቡ የአጥምቁን ጥያቄ ምላሽ መስጠት አልቻለም ነበር፡፡
ለዚህም ይመስላል ቅዱስ ሲኖዶስ በ 1998 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶች ቦታው እራሱን የቻለ ጳጳስ እንዲኖረው በማመኑ ብፁዕ አቡነ እንባቆምን ጳጳስ አድርጎ በመሾም የላከው፡፡

ብፁዕ አቡነ እንባቆም ቅዱስ ሲኖዶስ የጣለባቸውን አላፊነት በፍፁም ትጋትና አላፊነት ለመወጣት በሀገረ ስብከቱ ሁሉም ወረዳዎች መኪና የሚሄድባቸውን ቦታዎች በመኪና ለመኪና ፍጹም አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎችን ደግሞ የረጅም ሰዓትና ቀናት የእግር ጉዞዎችን በማድረግ ሞተር ሳይክል በሚይገባባቸው ምቹ ያልሆኑ መንገዶችና መንደሮች እንደወጣት በሞተር ሳይክል በመፈናጠጥ በበቆሎ እና በፈረስ ጀርባ ለረጅም ሰዓት እየወደቁና እየተነሱ በመጓዝ ህዝቡን በቃለ እግዚአብሔር በማጽናናት ነገ ቤተክርስቲያን የሚሰራ ትውልድ እግዚእብሔር ሊያስነሳላችኃል በሚል ጽኑ ተስፋ የአከባቢውን ህዝብ በማሳመንና የመሰረት መስቀል በማስቀመጠ ለነገይቱ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሚሆኑ ዲያቆናት ካህናትና መምህራንን በመመልመል የአብነት ትምህርት እንዲማሩ በማድረግ ነገ ለሚታነጹ አዳዲስ አብያተክርስቲያናት ሰው በማዘጋጀት እንዲሁም ለሚሰሩት ቤተክርስቲያኖች ንዋየቅዱሳትን ከአዲስ አበባ በማሰባሰብና የምህመኑን ጥያቄ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ተጋድሎ ቢያደርጉም የሀገረስብከቱ ፍላጎትና ጥያቄ በእርሳቸው ትጋት ብቻ መመለስና ሟሟላት እንደማይቻል በመረዳታቸው በ2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዐቢይ ኮሚቴ እንዲቋቋም በማመናቸው በእርሳቸው አሰባሳቢነት በሀገረ ስብከቱና በጠቅላይ ቤተክህነት በጎ ፈቃድ አንድ ዐቢይ ኮሚቴ በአዲስ አበባ አንድ ንዑስ ኮሚቴ ደግሞ በጅንካ ከተማ አቋቁመዋል፡፡

የኮሚቴው ዋና አላማ ብጹዕ አቡነ እንባቆም የጀመሩትን የአብያተክርስቲያናት ግንባታ የስብከተ ወንጌል ማስፋፋትና የልማት ስራ መደገፍ መሆኑ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ልማት ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ተብሎ ተሰይሟል እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል፡፡

የኮሚቴውን የአምስት ዓመት እስትራቴጅክ ፕላን እና ዝርዝር የስራ ዕቅድ ለመመልከት እዚህ ይጫኑ ይቀጥላል፡፡