የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በሀገረ ስብከቱ እየተከሰተ ያለውን የካህናትና የዲያቆናት ችግር ለመቅረፍ 10 ወጣቶችን ከ16 ብሔረሰቦች ሰብስቦ አዲስ ወደ ተከፈተው ወልቂጤ ጉንቸሬ ከተማ ወደሚገኘው ካህናት ማሰልጠኛ አስገባ፡፡
ይህን ውጤታማ እንዲሆን ልጆቹን በመመልመል ደብዳቤ ማሰልጠኛውን በበላይነት ለሚመሩት ለብጹዕ አቡን ቀለሜንጦስ ደብደቤ በመጻፍ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ያደረገው እተዋጾዖ ቀላል ስላልነበር ኮሚቴው ሊያመሰግን ይወዳል፡፡
ኮሚቴው ከዚህ በፊት በጸርዓ ጽዮን ማሰልጠኛ 10 ለድቁና ትምህርት አስተምሮ ያስመረቀ ሲሆን አሁንም 10 ተማሪዎች ለድቁና ደብረ ሊባኖት በመስተማር ላይ ይገኛል፡፡በደብረ ሊባኖስ የሚገኙት ተማሪዎች ውዳሴ ማርያም መልክዐ ማርያም መልክዐ ኢየሱስ ግብረ ድቁና አጠናቀው ሰዓታት እየተማሩ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ነገ ወደብሔረሰባቸው ሲሄዱ ሌሎች ብዙ ዲያቆናት ሊያፈሩ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
አሁን ጉንቸሬ የገቡት ለሶስተኛ ዙር እንደሆነ እና ይህ ተግባር ተጠናክሮ ከቀጠለ የሀገረ ስብከቱ የካህናት ችግር ለመቅረፉ አይነተኛ መፍትሄ ሊሆን እንደሚችል የማህበሩ አማራር አባላት ተናግረዋል፡፡እግዚአብሔር ተማሪዎቹ ያስፈጽምልን፡፡



