ኦርቶዶክስ መነኩሴ ናት በስሟ የተመሠረተ የበጎ አድራጎት ድርጅት አላት ድርጅቷ በዓለም አፍጋኒስታንን ጨምሮ በ43 ሀገሮች ይሰራል።

በአራት የተለያዩ ዲሲሊኖች ቴዎሎጅ ወይም ነገረ መለኮት ጨምሮ ማስተርሶች አሏት። የኢየሱስን ቋንቋ (language of the Jesus christ ) አራማይክን ጨምሮ 14 ቋንቋዎችን ትናጋራለች። ትውልዷ ሶርያ ቢሆን አክራሪ ሙስሊሞች አይ ኤር ባደረሰባቸው ግፍ ተሰደው ጀርመን ይኖራሉ። የስሟ ትርጓሜ ማርያም ማለት ነው። ቤተሰቧ ውስጥ አራት ሴቶች አሉ የአራቱም የስማቸው ትርጉም ማርያም ማለት ነው በተለያዩ ቋንቋዎች ጠንካራ የሶርያ ክርስቲያን ነች።
ሲስተር ሃቱኔ ኢትዮጵያ ለአምተኛ ጊዜ መምጣቷ ነው በተለይ ባለፈው በአክራሪ ሙስሊሞች የተቃጠሉት አብያተክርስቲያናትና በኦርቶዶክሳዊያን ላይ የደረሰውን ግፍ ጅጅጋ ቦታው ድረስ ሄዳ አይታለች አልቅሳለች። በተለያዪ የአውሮፖ ዩኒቨርሲቲዎች እየተጋበዘች በሶርያዊያንና በሌሎች ክርስቲያኖች እደረሰ ያለውን በደልና ግፍ ትናገራለች 12 መጽሐፍት ጽፋለች። አንዱ መጽሐፏ በሽያጭ ደረጃ በአውሮፖ በአንደኛ ደረጃ ሆኖ አነጋጋሪ ሆኖ ተመዝግቧል። ትላንት ቅዱስ ፖትሪያርክ አቡነ ማትያስ ጋር ቀጠሮ አስይዛ ገብተን እያለቀሰች በጅጅጋ ስላየችው አሳዛኝ ግፍ እና በቀጣይ ቤተክርስቲያኒቱ ልታደርግ በሚገባው ጉዳይ ላይ በእንባ ጭምር አስረድታለች።
አሁን ደቡብ ኦሞ በመጠመቅ ላይ የሚገኙ 16ቱን ብሔረሰቦች በተለይ ሐመርን እና የኬንያ ጠረፍ ጠባቂዋን ቅድስት ኪዳነምህረትን ለመጎብኘት ከእኔ ጋር ጅንካ ተገኝታለች ለምንኩስናዋ ምክንያት ስለሆነው ቅዱስ አግናጥዎስ ምጥው ለአንበሳ እና ስለሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ተናግራ አትጠግብም።
በደቡብ ኦሞ ኮሚቴ አስተባባሪነት የሚገነባውን የአብነት ትምህርት ቤትና ተማሪዎች የእርሻ ልማቱን እየጎበኘች ነው። ስለዚህች ጠንካራ መነኩሴ ብዙ ምላችሁ ይኖረኛል።
ሌላው አስደናቂ ነገር የሐመር ሰንበቴ በሐመር ሻንቆ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ ተጠማቅያን ባላቸው ተሰልፈው ሰንበቴ/ጸበል ጸሪቅ ጀምረዋል። ከአዲስ አበባ ያጣነውን እዚህ በማግኘታችን ደስታችን ወደር አልነበረውም። እኔ ግን ስገምት የነገዋን ቤተክርስቲያን የሚታደጓት እኚህ ሳይሆኑ አይቀሩም ምክንያቱ በከተማ ካቴድራሎች የገንዘብ ብዛትና የህንጻ ውበት ብቻ እየሆኑ መንፈሳዊ ዕሴቶቻቸው አውጥተው እየጣሉ ነውና።
በቀሲስ አበባየሁ ፍቃዱ






