እንኳን ደስ አላችሁ

የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታችን የመጀመሪያው ፎቅ እስላብ ሙሌት በድል ተጠናቋል።እግዚአብሔር ይመስገን

***//***

በዚህ ታላቅ ታሪካዊ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁና በመሳተፍ ላይ ያላችሁ ምስጋና ይገባቾኃል።አትሮንስ የግንባታው ንኡስ ክፍል የጅንካው ንኡስ ኮሚቴ እና የኮሚቴያችን ደጋፊዎቻችን በተለይም ግሸን ብረታብረት ወንድማችን አቶ አስቻለው አምናችሁ ከጉድለታችሁ የሰጣችሁን ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁእነሆ ገንዘባችሁ ብልና ነቀዝ በማያበላሸው በሰማያዊው መዝገብ ውስጥ ተከማቸላችሁ በሰማያዊት አምሳል በኢየሩሳሌም ህያው ምስክር ሊሆን ቆመላችሁ።እንኳን ደስ አላችሁ።የጦርነትና የሞት ሰበር ዜና ብቻ በሚሰማበት ለነፍሳችን መጽናኛ መልካም ወሬ ያሰማህንና የምታሰማን አምላከ ተክለሃይማኖት እናመሰግንሃለን።በሉ በጅንካ እና በአከባቢው ያላችሁ በታችኛው የፊኒሽግ ሥራ ላይ ተረባረቡ እና እነዚህ የሐመር የበና የጸማይ የሙርሲ የማሌ …የብሔረሰቡ ልጆች ገብተው ተምረው ሃይማኖት ያጽኑ ተዋህዶን ይስበኩ በድል ይሻገሩያልተጠመቁትን አጥምቁን የሚሉትን ያጥምቁ በሉ በሉ ፍጠኑበሆነውና በሚሆነው ሁሉ ልኡል አባታችን እግዚአብሔር እናመሰግንሃለን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *