ዜና ሲመተ ክህነት

በጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም እና በተለያዩ አጥቢያዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ ቆይተው ለሲመተ ክህነት የሚያበቃቸውን የአብነት ትምህርት ያጠናቀቁ ደቀ መዛሙርት 65 ዲያቆናት እና 8 ቀሳውስት በትላንትናው ዕለት ከብፁእ አባታችን አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አንብሮተ እድ በጂንካ አንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ተሹመዋል ።

በዕለቱም ብፁእነታቸው አባታዊ መመሪያና ቃለ ምዕዳን በመስጠት በሃገረ ስብከቱ ብቸኛ የሆነውን የጻድቁን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በመንፈሳዊ ይዘቱና አገልግሎቱ ዳግማዊ ደብረ ሊባኖስ እንዲሆን በተጠናና በተጠናከረ ሁኔታ መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል ።

በየአጥቢያው ያለውን አገልግሎት ለማጠናከር እንዲረዳ በማዕረገ ዲቁና እና በማዕረገ ቅስና ክህነት የተሾሙ እነዚህ ደቀ መዛሙርት ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎት እድገት ትልቅ አስተዋፅኦን የሚያደርጉ በመሆኑ ፤ እናንተም ዲያቆናት እና ቀሳውስት በተሰጣችሁ የመንፈስ ቅዱስ ኃላፊነት ታምናችሁ ቤተ ክርስቲያኗን እና ሕዝበ ክርስቲያኑን በትጋት እንድታገለግሉ አደራ እያልን የአገልግሎት ዘመናችሁንም ቅድስት ሥላሴ እንዲባርኩልን ጸሎታችን ነው። 

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

ምንጭ ጅንካ ሥላሴ ሰ/ት/ቤት