አብያተ ክርስቲያናት ተመረቁ

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያና ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ የተገነቡ አብያተክርስቲያናት ተመረቁ፡፡ በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሶስት አብያተክርስቲያናት ተመሩቀ፡፡ አብያተክርስቲያናቱን የመረቁት የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ቡጹዕ አቡነ እንባቆም ናቸው፡፡

የተመረቁት አብያተክርስቲያናት 1. በካቲባኮ ቅድስት ሥላሴ በሰኔ 4/2008 ዓ.ም ተመርቆ – 188 ምህመናን ተጠምቀዋል 2. ማሌ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲን በሰኔ 5/2008 – 186 ምህመናን ተጠምቀዋል 3. በቡብ አሪ ወረዳ በዘመር ቅዱስ አማኑኤ ቤተክርስትያን በሰኔ 6/2008- 537 ምህመናን ተጠምቀዋል

Continue reading “አብያተ ክርስቲያናት ተመረቁ”

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ 1998 እስከ 2005 ዓ.ም

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከመዲናችን አዲስ አበባ 780 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በእጅጉ ቆላማ የሆነ እና ሁሉም የየራሳቸው የሆነ መገለጫ ቋንቋ፣ ባህል፣አለባበስ፣ አመጋገብ የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው የ16 ብሔረሰቦች መናኸሪያ ከመሆኑም ባሻገር መልክዐ ምድሩ እንደሰንሰለት የተያያዙና የተሰናሰሉ ተራሮች የሚበዙበት በቀላሉ በመኪና የማይደፈር ሀገረ ስብከት ነው፡፡

Continue reading “የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ 1998 እስከ 2005 ዓ.ም”

ራዕይ፤ ተልዕኮ፤ እሴት፤ አላማዎች

ራዕይ (Vision)

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችና አጎራባች አካባቢዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ሥርዓት ተስፋፍቶና ተጠናክሮ ማየት

ተልዕኮ (Mission)

  • በሀገረ ስብቱና አጎራባች አካባቢዎች ላይ የወንጌል አገልግሎትን ማጠናከርና  ማስፋፋት
  • ከሕብረተሰቡ እየተነሱ ባሉት ጥያቄዎች መሠረት በሀ/ስብከቱ ያሉትን የአብያተ ክርስትያናት መጠን በበቂ ቁጥር ማሳደግ
  • የሃገረ ስብከቱን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ለማጠናከርና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ተግባራትን ማከናወን፡
Continue reading “ራዕይ፤ ተልዕኮ፤ እሴት፤ አላማዎች”