ታላቅ አውደ ርእይ በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ገዳም

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አትሮኖስ የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ ክፍል ያዘጋጅው ዐውደ ርእይ ነሐሴ 11 ቀን 2009 ዓ.ም በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ቅድስት ኪዳነ ምህርት የገደሙ አለቃ ተባርኮ ተከፈተ።

አውደ ርእይ እስከ ነሐሴ 15 2009 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ በመሆኑ እንድትጎበኝ ተጋብዛችኃል፡፡

በነምረሙዝ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን 2000 በላይ ኢአማንያንን ተጠመቁ

የደቡብ ኦሞ ኮሚቴ ከሐምሌ 15-22/2009 ዓ.ም ባደረጉው መንፈሳዊ ጉዞ በነምረሙዝ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን 2000 በላይ ኢአማንያንን አጠመቀ።

Continue reading “በነምረሙዝ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን 2000 በላይ ኢአማንያንን ተጠመቁ”

ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ለደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ፓትርያሪኩና በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተሹመዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው በአለ ሲመት ለደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት አባ ፊሊጳስ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ተብለው በቅዱስ ፓትርያሪኩና በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተሹመዋል፡፡ እኛም ከጠቅላይ ቤተክህነት ያገኘነውን የብጹዕ አቡነ ፊሊጶስን አጭር የሕይወት ታሪክ እነሆ ብለናል፡፡

Continue reading “ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ለደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ፓትርያሪኩና በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተሹመዋል፡፡”

ደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት የራሱ ሊቀ ጳጳስ ተመደበለት

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ብጹዕ አቡነ ዕንባቆም ሀገረ ስብከቱ ከለቀቁበት ጊዜ ጀምሮ ከሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጋር በተደራቢነት ሲተዳደር መቆየቱ ይታወሳል፡፡በዘንድሮ በዓለ ሲመት ሲመት ከሚሾሙቱ ዕጩ ኤጴሲ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት አባ ፊሊጶስ ለሀገረ ስብከቱ መመደባቸውን ለማወቅ ተችሏል። የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባወጣውም የስም አሰያየም “አባ ፊሊጶስ” የጵጵስ ስማቸውም “ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ” እንዲሆን መወሰኑም ተሰምቷል።

ለብጹዕ አባታችን መልካም የሥራ ዘመን እንመኛለን።

ለአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ገለጻ ተደረገ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባለፈው ሳምንት ማለት ከሰኔ 19-23, 2009 ዓ.ም ለአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ ነበረውን ሥልጠና በሚያጠናቅቅበት ዕለት 30 ደቂቃ የደቡብ ኦሞን የ16ቱ ብሔረሰቦችን መንፈሳዊ ፍላጎት ሁሉም እንዲረዳው ብሎም ወደ አድባራቱና ገዳማቱ በሚወረድበት ጊዜ ተገቢው የሆነ ትብብር እንዲደረግለት ገለጻ እንዲደረግ በማዘዙ በሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ በመ/ር ጎይቶም ያየኑ መልካም ፈቃድ ገለጻው ተደርጓል።

Continue reading “ለአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ገለጻ ተደረገ”

ዐውደ ርዕይ በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተካሄደ

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከት ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የ4 ቀን ዐውደ ርዕይ አካሄደ፡፡ዐውደ ርዕዩ ከሰኔ 17-20, 2009 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን ከ5,000 በላይ ምዕመናን ተመልክተውታል፡፡ዐውደ ርዕዩን  ከሌሎቹ ዐውደ ርእዮች ልዩ የሚያደርገው የመክፈቻው ዕለት የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ገ/ሚካኤል ስለ 16 ብሔረሰቦች በቂ ማብራሪያና ንግግር ካደረጉ በኃላ የቅዳሴው ማሳረጊያ ሰርሆተ ህዝቡ በዐውደ ርእይው ድንኳን እንዲሆን መደረጉ ነው፡፡

Continue reading “ዐውደ ርዕይ በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተካሄደ”

ዜና – የካህናትና የዲያቆናት ሥልጠና

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ በሀገረ ስብከቱ እየተከሰተ ያለውን የካህናትና የዲያቆናት ችግር ለመቅረፍ 10 ወጣቶችን ከ16 ብሔረሰቦች ሰብስቦ አዲስ ወደ ተከፈተው ወልቂጤ ጉንቸሬ ከተማ ወደሚገኘው ካህናት ማሰልጠኛ አስገባ፡፡
ይህን ውጤታማ እንዲሆን ልጆቹን በመመልመል ደብዳቤ ማሰልጠኛውን በበላይነት ለሚመሩት ለብጹዕ አቡን ቀለሜንጦስ ደብደቤ በመጻፍ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ያደረገው እተዋጾዖ ቀላል ስላልነበር ኮሚቴው ሊያመሰግን ይወዳል፡፡

Continue reading “ዜና – የካህናትና የዲያቆናት ሥልጠና”

የ2009 ዓ.ም የየካቲት የጉዞ ማስታወሻ

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከት ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ዘንድሮም እንደ ከርሞ ሁሉ ወደ ነምረሙዝ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ያደረገውን ጉዞ በሰላም አጠናቆ የካቲት 20 ቀን 2009 ዓ.ም አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

የዘንድሮውን ጉዞ ልዩ የሚያደርገው የጠቅላይ ቤተክህነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቴሌቨዥን ፕሮግራም ጉዞውን ለመዘገብ ጋዜጤኞች አብረው መጓዛቸው ነበር፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በቅርብ ሰፊ ዘገባ ሀገረ ስብከቱን አስመልክቶ እንጠብቃለን፡፡

Continue reading “የ2009 ዓ.ም የየካቲት የጉዞ ማስታወሻ”

የምረቃ ዜና

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ አስተባባሪነት በደቡብ ኦሞ  አምስት አብያተክርስቲያናት ተመርቀዋል፡፡ ኮሚቴው ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠው ፈቃድ የደቡብ ኦሞ ኮሚቴን እንዲደግፍ እዚህ  አዲስ አበባ ላይ እየተንቀሳቀሰ ያለ ሲሆን ከዚህ በፊት በደቡብ ኦሞ የሚገኙ የ16 በላይ ብሔረሰቦች ውስጥ 33 አብያተክርስቲያንን ያስገነባ ሲሆን አሁን ያስመረቃቸው አምስት አዳዲስ አብያተክርስቲያናት ኮሚቴው ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ያሳነጻቸውን አብያተክርስቲያናት ቁጥር 38 አድርሶታል፡፡

Continue reading “የምረቃ ዜና”

አስደሳችና ድንቅ ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እነሆ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህጻና ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ጥቅምት 19 ቀን በ2009 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ ኦሞ ቋንቋዎች በአሪኛ በሐመርኛ እና በማሌኛ ያዘጋጀውን መንፈሳዊ የመዝሙር ሲዲ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት የጠቅላይ ቤተክህነት ልዑካንና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ያስመርቃል፡፡

Continue reading “አስደሳችና ድንቅ ዜና”