የሰልጣኞች ምርቃት

የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ልማትና ህንጻ ቤተክርስቲያን አሰሪ ኮሚቴ ከነሀሴ 22-27/2009 ዓ.ም ለስድስት ቀን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ያሰለጠናቸውን 84 ወጣቶች አስመረቀ፡፡

ይህ ስልጠና በደቡብ ኦሞ በቋንቋ ለሚሰብኩ ወጣቶች የተዘጋጀ የማነቃቂ ስልጠና እንደሆነ የንኡስ ኮሚቴው ሰብሰባ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው ለሀገረ ስብከቱ ብቻ በሆነው አንቀጸ ብጹአን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የተሰጠ ሲሆን አሰልጣኞቹን ከአዲስ አበባ ልማድ ካላቸው ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲሁም ከጽርዓ ጽዮን ማሰልጠኛ ተቋም የተወጣጡ ነበሩ፡፡

ስልጠናው በተጠናቀቀበት ወቅቱ ሰልጣኞቹ አስተያያት ሲሰጡ ይህ ለእኛ ትልቅ ትጥቅ ነው አንድ ጊዜ ብቻ ተደርጎ የሚቋረጥ እንዳይሆን በየጊዜው መቀጠል ያለበት ስልጠና ነው ብለዋል፡፡
ነሀሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ተማሪዎቹን ባስመረቁበትና ለምስክር ወረቀት በሰጡበት ቀን ለተማሪዎቹ ቃለ ቡራኬ ሲሰጡ የተሰጣቸውን አደራ አጥብቀው በመያዝ የተማሩትን ትምህርት ለሌሎቹ በትጋት ማካፈል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ውዳሴ ማርያም አጠናቀው ለድቁና ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ከመካከላቸው በመመምረጥ ለ65 ተማሪዎች ማዕረገ ዲቁና ለ8 ዲያቆናት ደግሞ የቅስና ማዕረግ ሰጥተዋል፡፡