ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ለቋንቋ መምህራን የሁለት ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

በደቡብ ኦሞ ለሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ለቋንቋ መምህራን የሁለት ቀን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ኮሚቴ አስተባባሪነት የማንቂያ ደወል ስልጠና ከህዳር 7-8/2013 ዓ.ም በጅንካ ተሰጠ፡፡

ስልጠናው ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማንቃትና ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ አገልግሎ መስጠት የሚችሉበትን ሥራ መስራት እና የእርስ በእርስ ትስስርን ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ነበር፡፡

በስልጠው የምዝጊያ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ መንክራት ቆሞስ አባ ስምረት አብ ባስተላለፉት መልእክት ሰልጣኞቹ የተሰጣቸውን ስልጠና ተጠቅመው ሌሎችን ደግሞ በየሰንበት ትምህርት ቤቱ ማንቃት እንዳለባቸውን ወቅቱን ያገናዘበ ስልጠና በእዚህ መልክ ኮሚቴ በተከታታይነት ማዘጋጀት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ

የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታችን የመጀመሪያው ፎቅ እስላብ ሙሌት በድል ተጠናቋል።እግዚአብሔር ይመስገን

***//***

በዚህ ታላቅ ታሪካዊ ሥራ ላይ የተሳተፋችሁና በመሳተፍ ላይ ያላችሁ ምስጋና ይገባቾኃል።አትሮንስ የግንባታው ንኡስ ክፍል የጅንካው ንኡስ ኮሚቴ እና የኮሚቴያችን ደጋፊዎቻችን በተለይም ግሸን ብረታብረት ወንድማችን አቶ አስቻለው አምናችሁ ከጉድለታችሁ የሰጣችሁን ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁእነሆ ገንዘባችሁ ብልና ነቀዝ በማያበላሸው በሰማያዊው መዝገብ ውስጥ ተከማቸላችሁ በሰማያዊት አምሳል በኢየሩሳሌም ህያው ምስክር ሊሆን ቆመላችሁ።እንኳን ደስ አላችሁ።የጦርነትና የሞት ሰበር ዜና ብቻ በሚሰማበት ለነፍሳችን መጽናኛ መልካም ወሬ ያሰማህንና የምታሰማን አምላከ ተክለሃይማኖት እናመሰግንሃለን።በሉ በጅንካ እና በአከባቢው ያላችሁ በታችኛው የፊኒሽግ ሥራ ላይ ተረባረቡ እና እነዚህ የሐመር የበና የጸማይ የሙርሲ የማሌ …የብሔረሰቡ ልጆች ገብተው ተምረው ሃይማኖት ያጽኑ ተዋህዶን ይስበኩ በድል ይሻገሩያልተጠመቁትን አጥምቁን የሚሉትን ያጥምቁ በሉ በሉ ፍጠኑበሆነውና በሚሆነው ሁሉ ልኡል አባታችን እግዚአብሔር እናመሰግንሃለን

ቡስካ ተራራ ላይ

ቡስካ ተራራ ላይ በእግዚአብሔር ቸርነት የሚገርም ገዳም ተገድሟል ጥንታዊ አጸዶች መለያው የሆነ ቦታ ነው።ገዳሙ የኢትዮጵያዊው ቅዱስ የአቡነ ሙሴ ጸሊም ነው። የቤተክርስቲያ ግንባታ ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ ለእነህ ምስኪን እና የዋአን ህዝቦች ፈዋሽ ጸበል ፈለቀላቸውና በብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ተባርኮ እነሆ ለፈውስ ሆኗል።ጅንካ ዲመካ ቱርሚ ኦሞራቴ እና አከባቢው ያላችሁ ከሰሜን መጥተው ቦታው ከመጨናነቁ በፊት ተጠቀሙበት።የገዳሙ ቤተክርስቲያን ምረቃ በቅርብ ቅዱስ ፖትርያርኩ እና ብጹአን አባቶች በተገኙበት ይከናወናል ተዘጋጁተዋህዶ በቅዱሳን ጸሎት ታብባለችማን ያስባል በእንዲህ አይነት ቦታ እንዲህ ያለ ነገርስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን !!